5.1 እጩ አባል
1. ዕድሜው 18 ዓመትና ከዚያም በላይ የሆነ፣ የድርጂቱን ዓላማዎችና እምነቶች የተቀበለና ለተግባራዊነታቸውም ለመታገል ዝግጁ የሆነ፣
2. የድርጂቱን መዋጮ ለመክፈልና ሌሎች ግዴታዎችን ለመወጣት ፈቃደኛ የሆነ፣
3. አማራ የሆነ ፣በሃይማኖት፣ በፆታ፣ በቀለም ወይም በማንኛውም ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ መመዘኛ በወገኖቹ መካከል ልዩነት የማያደርግ፣
4. የአማራ ነጻ መንግስት ምስረታን የሚቀበልና በአማራ እውነተኛ ዲሞክራሲያዊ ሥርዓት እንዲሰፍን ለመታገል የወሰነ፣ ማንኛውም አማራ የድርጂቱ አባል ለመሆን የድርጂቱን አባልነት ማመልከቻ ቅጽ ሲሞላ ይህን ተግባር እንዲያከናውን ሀላፊነት የተሰጠው አካል ተቀብሎ ጥያቄውን ያስተናግዳል፡፡
5. በእጩ አባልነት ለመመዝገብ የፈለገና መስፈርቱን የሚያሟላ ማንኛውም አማራ ከዚህ በታች የተገለፀውን የትግል ቃልኪዳን ይህን እንዲያደርግ ስልጣን በተሰጠው አካል ቃል ኪዳን እንዲገባ ይደረጋል፡፡
እኔ ————————————— የቤተ አማራ ድርጅት አባል ስሆን በወገኔ ላይ እየደረሰ ያለዉን ዘር ማጥፋት ለመመከት እንዲሁም የአማራ ህዝብ ነፃ መንግስት ምስረታን እዉን ለማድረግ ተግቸ ልሰራ በግፍ ህይወታቸዉን ባጡ አማራ ወገኖቸ ስም ቃል እገባለሁ፡፡
5.2 ሙሉ አባል
1. በድርጅቱ እጩ አባል ሆኖ ከተመዘገበበት ቀን ጀምሮ እስከ ስድስት ሳምንት መጨረሻ ድረስ የእጩ አባልነት ግዴታውን በአግባቡ የተወጣ ዕጩ አባል የድርጅቱ ሙሉ አባል ይሆናል፡፡ ከስድስተኛው ሳምንት በኋላ በሚመለከተው አካል መልስ ካልተሰጠው ሙሉ አባል እንደሆነ ይቆጠራል፡፡
2. በድርጅቱ የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ተጠይቆ አባል ለመሆን ፈቃደኝነቱን የገለፀ አማራ በስራ አስፈፃሚ ኮሚቴው ውሳኔ መሰረት የተጠቀሰውን ጊዜ ሳይጠብቅ የድርጅቱ ሙሉ አባል ሊሆን ይችላል፡፡
5.3 ተባባሪ አባል፣
1. ዕድሜው ከ18 ዓመትና ከዚያ በላይ የሆነ፣ ከአዕምሮ ህመም ነፃ የሆነና በትግሉ ለመሳተፍ ዝግጁ የሆነ፣ ነገር ግን በሙሉ አባልነት ለመስራትና ለመንቀሳቀስ የጤና ችግር፣ የጊዜ እጥረትና የቦታ አለመመቻቸት ያጋጠመው ማንኛውም አማራ ተባባሪ አባል ሊሆን ይችላል፤
2. ተባባሪ አባላት ለድርጂቱ ሃላፊነት ቦታ ለመምረጥና ለመመረጥ እንዲሁም በድርጂቱ ውሳኔዎች ላይ ድምጽ ለመስጠት ካለመቻል በስተቀር ሌሎች የአባልነት መብቶች ሁሉ ይኖሯቸዋል፡፡
አንቀጽ 6፡- የአባልነት መብትና ግዴታ፣
6.1 መብት
1. በድርጂቱ ስብሳባዎች ሃሳብ የማቅረብና ድምጽ የመስጠት፣
2. ማንኛውም የድርጂቱ ሙሉ አባል የመምረጥና የመመረጥ መብት አለው፤ ማንኛውም ሙሉ አባል አኩል ድምፅ አለው
3. የድርጂቱ መተዳደሪያ ደንብና ፕሮግራም መከበሩን የመከታተል፣ ማንኛውም አባል ያለማንም ጣልቃገብነት ሃሳቡን በፈለገው መንገድ የመግለጽ መብት አለው
4. በራስ ተነሳሽነት አዳዲስና ጠቃሚ ሃሳቦችን የማፍለቅ፣ ለፓርቲ አመራር የማስተላለፍ፣
5. በድርጂቱ እንቅስቃሴዎችና ተግባሮች የመሳተፍ፣ ድርጅታዊ መዋቅርን ጠብቆ ስለድርጂቱ አሰራር ማብራሪያና መረጃ የመጠየቅና ሂስ የማቅረብ መብት አለው፡፡
6. ማንኛውም አባል በድርጂቱ የተለያዩ እንቅስቃሴዎች ውስጥ የመሳተፍ መብት አለው፡፡ 7. ማንኛውም አባል በራሱ ፍላጎት አባልነቱን የመተው መብት አለው፡፡
6.2 ግዴታ
1. የድርጂቱን ዓላማና ፕሮግራም ተግባራዊ ማድረግ፣ ለህዝብ ማስተዋወቅና ማሰራጨት፣
2. የድርጂቱን መተዳደሪያ ደንብና መመሪያዎች ማክበርና የድርጅቱን አመራር ውሳኔዎች ተግባራዊ ማድረግ፣
3. በተለያዩ ቋሚና ጊዜያዊ ኮሚቴዎችና፣ ድርጅቱ በሚጠራቸው የተለዩ ስብሰባዎች መሳተፍ፣
4. የአባልነት መዋጮን በወቅቱ መክፈልና በድርጂቱ የገንዘብ መዋጮ ተግባራት መሳተፍ፣
5. የአባላት ክፍያ የድርጅት አባልነት ዝቅተኛው መስፈርት መሆኑን አውቆ የድርጅት ወርሃዊ መዋጮ በጊዜው መክፈል ያልቻለ በሚቀጥለው የክፍያ ጊዜ እጥፍ አድርጎ እንዲከፍል ይደረጋል። ይህን ማድረግ ያልቻለ አባል ግን ለዲሲፕሊን ኮሚቴው ቀርቦ ውሳኔ እንዲሰጥበት ይደረጋል።
6. የድርጂቱን ዓላማ ከሚጎዱ ማናቸውም እንቅስቃሴዎችና የሥነ-ምግባር ጉድለቶች መቆጠብ፣ 7. ለድርጂቱ ታማኝ መሆንና ሚስጥር መጠበቅ፣
8. መለያየትና መከፋፈልን ከመፍጠር ራስንና ሌሎችን ማራቅ፣
የቤተ-አማራ የአባላት ፎርም (pdf)
Download